
The Ethiopian Civil Society Organizations Council (ECSOC) hosted a ceremony honoring its outgoing Executive Committee (ExCom) Members.
In the recognition ceremony, the Council celebrated the former ExCom’s dedication, hard work, and invaluable contributions to the Council and the broader CSO sector.
The event also provided a platform for former ExCom members to share their experiences and inspire the new leadership to continue the important work ahead.
ECSOC’s President Ahmed Hussen, who was also recognized for his role as Vice President during the previous tenure expressed his gratitude for the outgoing leadership’s invaluable efforts and dedication starting from the Council's inception.
Meanwhile, Executive Director of the Council, Terefe Degeti commended the former ExCom members for their determination through challenging times.
Former President of the Council, Dr. Nigussu Legesse thanked ECSOC for the recognition and pledged ongoing support.
On the other hand ACSO's Director General Samson Biratu reiterated the Authority’s commitment to standing by the Council for the betterment of Ethiopia’s CSO sector.
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የቀድሞ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቱን የክብር እና የምስጋና ሥነ ስርዓት አዘጋጀ።
በእውቅና ሥነ-ስርዓቱ ላይ ምክር ቤቱ የቀድሞ የአመራር አባላት ቁርጠኝነት፣ ታታሪነት እና ለምክር ቤቱ እና ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፉ ያበረከቱት አስተዋጾን አመስግኗል። በመድረኩ የቀድሞ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ልምዳቸውን ያጋሩበት እንዲሁም አዲስ በኮሚቴው ለተቀላቀሉ አመራር በቀጣይ የሚጠበቀውን ቁልፍ ስራ እንዲቀጥል የሚያበረታታ ዝግጅት ተከናውኗል።
የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ አህመድ ሁሴን በቀድሞው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በምክትል ፕሬዝደንትነት ሚናቸው እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን ባስተላለፉት መልዕክታቸው ከምክር ቤቱ ምሥረታ አንስቶ የቀድሞ አመራሮቹ ላደረጉት የላቀ አስተዋጾ እና ያለመታከት ላሳዩት ትጋት ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የምክር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተረፈ ደጌቲ የቀድሞ የስራ አስፈፃሚ አባላት በአስቸጋሪ ጊዜያት ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበው በርካታ ስራ ወደፊት የሚጠበቅ መሆኑ በቀድሞ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የተጀመሩ በርካታ ስራዎች በሙሉ የሃገሪቱን የሲቪል ማህበረሰብ ዘርፍ አንድ እርምጃ ወደፊት እንዲራመድ ከፍተኛ አበርክቶ እንደነበረው አስምረውበታል።
የቀድሞ የምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ዶ/ር ንጉሱ ለገሰ ምክር ቤቱ ላደረገላቸው እውቅና አመስግነው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
በሌላ በኩል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ሳምሶን ቢራቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ዘርፍ እድገት ከምክር ቤቱ ጎን ለመቆም ያለውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።